Fana: At a Speed of Life!

የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ፖሊሲ በአዲሱ ዓመት ተግባራዊ እንደሚሆን ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 12 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አዲሱ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ፖሊሲ በ2013 ዓ.ም ተግባራዊ እንደሚሆን የኢኖቬሽንና ቴክኖሊጂ ሚኒስቴር አስታወቀ።
 
የሚኒስቴሩ የፖሊሲ፣ ስትራቴጂና ፊውቸር ፕላኒንግ ዳይሬክተር አቶ ደስታ አበራ ÷ አዲሱ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ፖሊሲ ረቂቅ ክለሳ አሁን ላይ የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ ደርሷል ብለዋል።
 
ረቂቅ ፖሊሲው በ2004 ዓ.ም የወጣው የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ፖሊሲ የአፈጻጸም ክፍተቶችን በጥናት በመለየት አሁን ያለውን አገራዊ ለውጥ ከግምት ማስገባቱን ገልጸዋል።
 
የአፈጻጸምና ፖሊሲ አቀራረጽ፣ አገር በቀል እውቀቶችን ታሳቢ አለማድረግ እና ተግባራዊ የሚደረግባቸው ዘርፎችን በግልፅ አለማስቀመጥ የ2004 ዓ.ም ፖሊሲ ከነበረበት ክፍተቶች ውስጥ መሆኑንም አቶ ደስታ ዘርዝረዋል።
 
በመሆኑም አለም ከደረሰበት ተለዋዋጭ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ስራዎች ጋር አብሮ የሚሄድ ፤ የልማትና ምጣኔ ሃብት እድገትን ለማፋጠን ክለሳ ማድረግ አስፈልጓል ነው ያሉት ።
 
ኢትዮጵያ አሁን ያለችበትን የለውጥና ምጣኔ ሃብት እድገት ደረጃ ሊሸከም የሚችል አለመሆኑ ሌላኛው የፖሊሲ ክለሳ ያስፈለገበት ምክንያት መሆኑን ሃላፊው ማስረዳታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
 
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.