Fana: At a Speed of Life!

የሴቶችን ችግር በንግግር እና በመፈክር ብቻ ሳይሆን በተግባር መፍታት ይገባል -ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 27 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ̎ትችያለሽ – በፈተና የተሞረደ ማንነት ለለውጥ የተመቸ ስብዕና ይገነባል!̎ በሚል መሪ ቃል በግንባታው ዘርፍ የተሰማሩ ሴቶችን ሚና፣ አቅምና አርአያነት የሚዘክር ሃገር አቀፍ የምክክር መድረክ በአዲስ አበባ ተካሄደ።
በመድረኩ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የሴቶች እኩልነት አጀንዳ የአዳራሽ ውስጥ የስብሰባ ማድመቂያ መሆኑ ቀርቶ እያንዳንዷ ቀን ቃል በተግባር የሚገለጽበትና የችግሩ ሳይሆን የመፍትሔው አካል መሆን የሚረጋገጥበት ሊሆን እንደሚገባ ተናግረዋል ።
የሴቶች ችግር በንግግርና በመፈክር ብቻ አይፈታም ያሉት ፕሬዝዳንቷ የተናገርናቸውንና ያቀድናቸውን በሙሉ ልንተገብር ይገባል ሲሉ ገልጸዋል ።
እንዲሁም ሴቶች በተለያዩ ዘርፎች ያስመዘገቧቸውን ስኬቶች እውቅና መስጠት እና ማበረታታት ይገባል ብለዋል ።
የውይይት መድረኩ በከተማ ልማት ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ የኮንስትራክሽን ስራዎች ባለስልጣንና የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን በጋራ የተዘጋጀ መሆኑ ታውቋል፡፡
በመድረኩ በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሴቶችን ሚና እና አርአያነት እንዲሁም በተለያዩ መስኮች ውጤታማ የሆኑ ሴቶች ልምድና ተሞክሯቸውን የሚያሳይ ዘጋቢ ፊልም እና የመነሻ ጥናቶች ከተለያዩ ምሁራን ቀርቦ ውይይት ወይይት መካሄዱን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-

https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.