Fana: At a Speed of Life!

የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ አመራሮች በቄለም ወለጋ የልማት ሥራዎችን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌዴራል እና የክልል ከፍተኛ አመራሮች በቄለም ወለጋ እየተሰሩ ያሉ የተለያዩ የልማትፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል፡፡

በጉብኝቱ  የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር  ሃብታሙ ኢተፋ (ኢ/ር)፣ የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዴዔታ ነመራ ገበየሁ (ዶ/ር) እና የጉሙሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ ተሳተፈዋል፡፡

እንዲሁም የጨፌ ኦሮሚያ ም/አፈ-ጉባዔ ኤሊያስ ኡመታ፣ በብልጽግና ፓርቲ የኦሮሚያ ክልል ቅርንጫፍ  የአደረጃጀት ዘርፍ ሃላፊ ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር) እና የዞኑ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡

በጉብኝታቸውም በቄጦ ወንዝ ላይ 10 ሺህ አባዎራዎችን ተጠቃሚ ያደርጋል የተባለውን የመስኖ ግድብ እንዲሁም ኢሉ አባቦርን ከቄለም ወለጋ ጋር የሚያገናኘውን የአስፓልት መንገድ ተመልክተዋል፡፡

በዚህም የቄጦ የመስኖ ፕሮጀክት ሥራ አሁን ላይ 32 በመቶ መድረሱ የተገለፀ ሲሆን፤ በ2017 ዓ.ም ህዳር ወር ይጠናቀቃል ተብሏል።

የፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ የዚህዓለም ክንዴ÷ፕሮጀክቱ በ2013 ዓ.ም ተጀምሮ በዲዛይን እና በተከሰተው የፀጥታ ችግር ምክንያት መጓተት ገጥሞት እንደነበር ገልፀዋል፡፡

አሁን ላይም ፕሮጀክቱን በተያዘለት ጊዜ ለመጨረስ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ነው የተናገሩት፡፡

ቄለም ወለጋን ከኢሉ አባቦር ያገናኛል የተባለው የአስፓልት መንገድም በፀጥታና በኮንትራክተሮች አፈፃፀም ማነስ ምክንያት መጓተት ተጠቁሟል፡፡

እነዚህን ችግሮች በማስተካከል ፕሮጀክቱ እንዲጠናቀቅ አቅጣጫ ተቀምጦ እየተሰራ መሆኑም ተገልጿል፡፡

በታሪኩ ለገሰ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.