Fana: At a Speed of Life!

ማንቸስተር ዩናይትድና ሊቨርፑል አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ32ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ማንቸስተር ዩናይትድና ሊቨርፑል ያደረጉት ጨዋታ 2 ለ 2 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቀቀ፡፡

የሳምንቱ ተጠባቂ በሆነው በዚህ ጨዋታ በሜዳው ለተጫወተው ማንቸስተር ዩናይትድ ብሩኖ ፈርናንዴዝ እና ማይኖ ጎሎቹን ሲያስቆጥሩ፤ ለሊቨርፑል ደግሞ ዲያዝ እና ሞሐመድ ሳላህ (በፍጹም ቅጣት ምት) አስቆጥረዋል።

ውጤቱን ተከትሎም ሊቨርፑል ከመሪው አርሴናል ጋር እኩል 71 ነጥብ ይዞ በጎል ክፍያ ተበልጦ ሁለተኛ ደረጃን ይዟል።

ነጥቡን 49 ያደረሰው ማንቸስተር ዩናይትድ ስድስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.