Fana: At a Speed of Life!

ሀገር ወዳድ የሆነ ምሁር ተቋም ያሻግራል፤ ሀገር ይገነባል – ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ በጥራት ፣ በብቃትና በልምድ ተመራጭ የሆነ ሃይል በማፍራት የመከላከያን ተልዕኮ እያሳለጠ ነው ሲሉ የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ተናገሩ።

ኢታማዦር ሹሙ ዩኒቨርሲቲውን በጎበኙበት ወቅት እንደገለጹት÷አዳዲስ የምርምር ግኝቶችን ፈጥሮ በመስራት የመከላከያ ሠራዊትን የትጥቅ አቅም በዘመናዊ ወታደራዊ የቴክኖሎጅ ውጤት የታገዘ እንዲሆን ማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡

በዚህ ረግድ የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ በጥራት ፣ በብቃትና በልምድ ተመራጭ የሆነ ሃይል በማፍራት የመከላከያን ተልዕኮ እያሳለጠ ይገኛል ብለዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው የመከላከያ ሰራዊቱን  ውስብስብ የግዳጅ ጉዞዎች ቀላልና ምቹ ማድረግ የሚችሉ የምርምር ሥራዎችን በመስራት ያበረከተውን አስተዋፅኦም አድንቀዋል።

ዩኒቨርሲቱው  በዘላቂ ጥናትና ምርምር የላቀ ውጤት በማምጣት ኢትዮጵያ በወታደራዊ ትጥቆች  እራሷን እንድትችል የተገኙ የምርምር ውጤቶችን ወደ ምርት ማስገባት እንዳለበት  አስገንዝበዋል፡፡

ተቋሙ ኢትዮጵያን በአፍሪካ ደረጃ ከፍ ማድረግ የሚችል አቃፊና ተፈላጊ ተቋም እንዲሆን ለማሥቻል የዩኒቨርሲቲው አመራሮች ፣የቦርድ አባላት ፣መምህራን እና ተመራማሪዎች በትብብር እንዲሰሩ አሳስበዋል፡፡

በጉብኝቱ ኢታማዦር ሹሙ የሰራዊቱን  የውጊያ አቅም ሊያሳድጉ የሚችሉ ያለቀላቸው የምርምር ሥራዎችን ተዘዋውረው መመልከታቸውን የመከላከያ ሰራዊት ማህበራዊ ትስስር ገጽ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.