Fana: At a Speed of Life!

የሶማሌ ክልል መንግሥት ለክልሉ ልዩ ሀይል ዘመናዊ ተሽከርካሪዎችን አበረከተ

አዲስ አበባ፣ ጥር 4፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል መንግሥት በክልሉ የሰፈነውን አስተማማኝ ሰላም የበለጠ ለማጠናከር ለክልሉ ልዩ ሀይል 78 ዘመናዊ ተሽከርካሪዎችን አበረከተ።
ክልሉ ካለው የተለያዩ መልከዓ ምድራዊ አቀማመጥ ጋር በተያያዘ ተሽከርካሪዎቹ የዜጎችን ሰላም ለማረጋገጥ አስፈላጊ እንደሆኑ ተገልጿል።
በአጠቃላይ በበጀት ዓመቱ ለክልሉ ሰላም መረጋገጥ ሲባል በ277 ሚሊየን ብር ወጪ 300 ዘመናዊ ተሽከርካሪዎች ተገዝተዋል ተብሏል፡፡
በመጀመሪያ ዙርም ወደ ሀገር ከገቡ 150 ተሽከርካሪዎች ውስጥ 78ቱ ዛሬ የሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ሀሰን መሀመድ ለሶማሌ ክልል ልዩ ሀይል ዋና አዛዥ ረዳት ኮሚሽነር መሀመድ አህመድ ማስረከባቸውን የሶማሌ ክልል ቴሌቪዥን ዘግቧል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.