Fana: At a Speed of Life!

የበጎ ፈቃድ አገልግሎት እና ወሰን ተሻጋሪ የወጣቶች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ማስጀመሪያ መርሐ ግብር እየተካሔደ ነው

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 20 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የክረምት ወራት የወጣቶች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት እና ወሰን ተሻጋሪ የወጣቶች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ማስጀመሪያ መርሐ ግብር በአዲስ አበባ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡
በመርሐ ግብሩ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን፣ የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ እንዲሁም ከፍተኛ የመንግስት ስራ ሃላፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡
የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ማስጀመሪያ መርሐ ግብርሩ ‘’በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ’’ በሚል መሪ ቃል ነው እየተካሔደ የሚገኘው፡፡
ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ÷በዘንድሮ የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት 19 ሚሊየን ወጣቶች በ12 የስምሪት መስኮች እንደሚሳተፉ መናገራቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ለፕሮግራሙ ስኬታማ ትግበራ ወጣቶች እና በየደረጃው የሚገኙ አስፈፃሚ አካላት የሚጠበቅባቸውን ሃላፊነት እንዲወጡ እና ለኢትዮጵያ ከፍታ በጎ አሻራቸውን እንዲያሳርፉም ጥሪ ቀርቧል።
 
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.