Fana: At a Speed of Life!

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከፍተኛ አመራሮች በወቅታዊ አገራዊ እና ክልላዊ ጉዳዮች ዙሪያ እየተወያዩ ነው

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 22 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ከፍተኛ አመራሮች በወቅታዊ አገራዊ እና ክልላዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ማካሄድ ጀምረዋል።
 
በውይይቱ የክልሉ ርዕሰ-መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሃሰን፣ የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኢሳቅ አብዱልቃድርን ጨምሮ የክልል ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም የዞንና የከተማ አስተዳደር አመራሮች ተሳትፈዋል፡፡
 
ውይይቱም እንደሃገር በተቀናጀ መንገድ የተካሄደው የመጀመሪያው ምዕራፍ የህልውና ጦርነት በድል መጠናቀቁን ተከትሎ ድሉን ዘላቂ በማድረግ የሀገሪቱን ብልጽግና ለማስቀጠል የጋራ አቋም የሚያዝበት መሆኑ ተጠቁሟል፡፡
 
በመድረኩም “ዘላቂ ድል ወደ ብልጽግና፣ የድህረ ጦርነት መዛነፎችና እርምጃዎች” የሚል መነሻ መወያያ ሠነድ ቀርቦ ውይይት እንደሚደረግብት ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
በህልውና ጦርነቱ ከተገኘው ድል ባሻገር የተጀመረውን ሁለንተናዊ የብልጽግና ጉዞ ለማረጋገጥ በድህረ ጦርነቱ ሊስተዋሉ የሚችሉ የተለያዩ ችግሮችን አመራሩ በተቀናጀና በአግባቡ ለመምራት የሚያስችል ግብዓት የሚገኝበት እንደሚሆንም ተገልጿል፡፡
 
የውይይት መድረኩ ከዛሬ ጀምሮ ለሶስት ተከታታይ ቀናት ነው የሚካሄደው፡፡
 
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.