Fana: At a Speed of Life!

የአሜሪካ ዓለም አቀፍ የልማት ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 11 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካ ዓለም አቀፍ የልማት ድርጅት (ዩ ኤስ አይ ዲ) ዋና ዳይሬክተር ሼን ጆንስ እና በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ አባላት መቐለ ከተማን ጎበኙ፡፡

በጉብኝቱ ወቅት ዋና ዳይሬክተሩ ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር፣ የአስቸኳይ ጊዜ አስተባባሪና ከሌሎች የፌደራልና የክልሉ የስራ ሃላፊዎች ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡

በዚህ ወቅትም የኤምባሲው አባላት አሜሪካ የመፍትሄ ሃሳቦችን ለይቶ በማቅረብ በአካባቢው የሚደረገውን ሰብአዊ ድጋፍ ለማሳደግ ብሎም ተጎጂዎችን ለመድረስ የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ ከአጋር አካላት ጋር በቅንጅት መስራቷን ትቀጥላለች ብለዋል፡፡

ጉብኝቱም በክልሉ ከተካሄደው የህግ ማስከበር ዘመቻ ጋር በተያያዘ አሜሪካ ሰብአዊና የአስተዳደር ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ በሚደረገው ጥረት የምታደርገውን ድጋፍ ለማጠናከር እንደሚያግዝም በዚህ ወቅት ተገልጿል፡፡

አሜሪካ በትግራይ ክልል የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥና ድህነትን ለመቀነስ የተለያዩ ድጋፎችን ስታደርግ ቆይታለች፡፡

በተያዘው የፈረንጆቹ 2021ም ለሰብአዊ ድጋፍና ልማት የሚውል ከ100 ሚሊየን ዶላር በላይ ድጋፍ እንደምታደርግም ዩ ኤስ አይ ዲ አስታውቋል፡፡

ገንዘቡ ስደተኞችን እና የሃገር ውስጥ ተፈናቃዮችን ለመደገፍ፣ ለአስቸኳይ የምግብ እርዳታና ድጋፍ፣ ለንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት፣ ለመጠለያ እና ለንጽህና መጠበቂያ እንደሚውልም ተገልጿል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.