Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለሉሲዎቹ እና ለአዲስ አበባ ከተማ ልዑካን የ5 ሚሊየን ብር ሽልማት አበረከተ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 5 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለሴቶች ብሄራዊ ቡድን እንዲሁም በአንደኛው ሃገር አቀፍ የኢትዮጵያ ወጣቶች ኦሊምፒክ ለተሳተፈው ለአዲስ አበባ ከተማ ልዑካን ቡድን ለእያንዳንዳቸው የ5 ሚሊየን ብር ሽልማት አበርክቷል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አበቤ በዛሬው ዕለት በአንደኛው ሀገር አቀፍ ወጣቶች ኦሊምፒክ ውድድር ላይ ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ የአዲስ አበባ የልዑካን ቡድን እና በሴካፋ ሴቶች ዋንጫ ላይ ሦስተኛ ደረጃ በመያዝ ላጠናቀቁት የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን (ሉሲዎቹ) የ5 ሚሊየን ብር ሽልማት አበርክተዋል፡፡

በዚህ ወቅት ከንቲባ አዳነች አቤቤ በሴቶች ብሔራዊ ቡድን እና ዋልያዎቹ በአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ግብፅ ላይ ከግማሽ ምዕተ ዓመት በኋላ ባስመዘገቡት ውጤት የተሰማቸውን ደስታም ገልጸዋል፡፡

የዋሊያዎቹ ቡድን በማጣርያው የታለመውን ግብ ሲያሳካ ከመስተዳድራቸው ሽልማት እንደሚጠብቀው ቃል መግባታቸውን ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡።

የኢትዮጵያ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን (ሉሲዎቹ) በሴካፋ ሴቶች ዋንጫ ላይ ተሳትፈው የነሐስ ሜዳልያ ተሸላሚ መሆናቸው ይታወቃል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.