Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ከተማ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ተወያየ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በድህረ ጦርነት ዝንፈቶችና በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ተወያየ፡፡

የውይይቱን መነሻ ሀሳብ ያቀረቡት የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ መለሰ ዓለሙ የፖለቲካ ፓርቲዎች ፉክክራቸው እንደተጠበቀ ሆኖ በጦርነቱ ወቅት ለመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ በማሰባሰብ እና የውጭ ጣልቃ ገብነቶችን የሚያወግዙ ፣ የህዝብ ንቅናቄዎችን በጋራ በመፍጠር በአንድነት በመቆም አገራቸውን መታደጋቸውን አስረድተዋል።

ጦርነቱ የህዝብን አንድነት ከማዳበሩም በተጨማሪ ኢትዮጵያን ለማዳን ከወትሮው በተለየ መልኩ የዳያስፖራውን ንቅናቄ መፍጠሩን ተናግረው የተከፈተው ጦርነት ብዙ የውስጥና የውጭ ሀገር ተዋናዮች ያሉበት ቢሆንም በአንድነት ከፍተኛ ድል አስመዝግበናል ብለዋል።

መንግስት እየወሰናቸው ያሉ ውሳኔዎች ሀገርን ለማስቀጠል ጠላቶቻችን ያጠመዱልንን ወጥመድ በመበጣጠስ የተገኘውን ድል ዘላቂ ማድረግን ዓላማው ያደረገ መሆኑን አቶ መለሰ አስገንዝበዋል።

በውይይቱ የተሳተፉ የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች በአጭር ጊዜ ውስጥ ምክር ቤቱ ጥሩ ውጤት ማስመዝገቡንና አገርን ለማዳን በተደረገው ጦርነት የድርሻችንን ተወጥተን የጋራ ድል አስመዝግበናል ያሉ ሲሆን፥ በቀጣይም የተጀመሩ የጋራ ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንደሚገባቸው ተናግረዋል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.