Fana: At a Speed of Life!

የአገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ ላይ ሁለተኛ ዙር ይፋዊ የህዝብ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 16 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ ላይ ሁለተኛው ዙር ይፋዊ የህዝብ ውይይት ተካሄደ፡፡
በውይይቱ የተገኙ ግብዓቶች እንደአስፈላጊነታቸው በአዋጁ ውስጥ እንደሚካተቱ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያገኘነው
መረጃ ያመላክታል፡፡
በውይይቱም የፍትህ ሚንስትሩ ዶክተር ጌዲዮዎን ጢሞቲዮስ የእጩ ኮማሽነሮችን ሹመት በተመለከተ በጠቅላይ ሚንስትሩ አቅራቢነት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንደሚፀድቅና ኮሚሽነሮቹ መሉ ጊዜያቸውን ስራ ላይ የሚያውሉ እንደሆነ አስረድተዋል።
አገራዊ የምክክር መድረኩ ዋና አላማ አገራዊ መግባባትን ለመፍጠር እስከሆነ ድረስ በርዕሱ ላይ ማሻሻያ ሊደረግበት
እንደሚችልም ሚኒስትሩ ጠቁመዋል።
የውይይቱ ተሳታፋዎች በበኩላቸው የሚቋቋመው ኮሚሽን የህዝብን አንድነት ለማስቀጠል እና አገሪቱ ከገባችበት ውስብስብ ችግር ማውጣት የሚያስችል መሆን እንዳለበት አንስተዋል።
ኮሚሽኑ ነጻና ገለልተኛ እንዲሆን በጀቱ ከገንዘብ ሚኒስቴር መውጣት እንዳለበት እና እጩ ኮሚሽነሮች በጠቅላይ ሚንስትር ይቀርባሉ የሚሉ ሀሳቦች ከረቂቅ አዋጁ ቢወጡ የሚሉ አስተያየቶችን ሰጥተዋል።
የኮሚሽኑ ኮሚሽነሮች ከፖለቲካ፣ ከሀይማኖት እና ከብሄር ወገንተኝነት የፀዱ፣ ችሎታቸው እና ብቃታቸው የተረጋገጠ፣
እንዲሁም አገርና ህዝብን ለማሻገር ቁርጠኛ የሆኑ ህዝብ ያመነባቸው ሊሆኑ እንደሚገባም ነው በውይይቱ የተነሳው።
አገር በቀል እውቀቶች እና እሴቶች በረቂቅ አዋጁ እና የረቂቅ አዋጁን ርዕስ አገራዊ የምክክር መድረክ ከማለት ይልቅ “ብሄራዊ የመግበባት መድረክ” ቢሆን የሚሉ ሃሳቦችን ታሳታፊዎቹ ማቅረባቸውን ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
የመጀመሪያው ዙር ውይይት ታህሳስ 11ቀን 2014 ዓ.ም መካሄዱ ይታወሳል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.