Fana: At a Speed of Life!

የአፍሪካ መሪዎች በፀጥታው ምክር ቤት ውስጥ አፍሪካ ቋሚ መቀመጫ እንዲኖራት ጠየቁ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 30፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) የሴኔጋል ፕሬዚደንት ማኪ ሳል እና የደቡብ አፍሪካው ፕሬዚደንት ሲሪል ራማፎሳ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ውስጥ 54 አገራትና 1ነጥብ 3 ቢሊየን ህዝብ ያላት አፍሪካ የተሰጣት ውክልና ኢፍትሃዊ መሆኑን ገለጹ።

የሴኔጋሉ ፕሬዚደንት ማኪ ሳል አፍሪካ ቢያንስ ሁለት መቀመጫዎችን በቋሚ አባልነት እንድታገኝ ከአፍሪካ ዉጭ ካሉ የፀጥታዉ ምክር ቤት አባላት ጋር ዉይይት እያደረጉ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ፕሬዚደንቱ በእርግጠኝነት መናገር የምንችለዉ 54 አገሮች ያሏት የአፍሪካ አህጉር የፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ አባል ሆና በቂ ዉክልና አለማግኘቷን ነዉ ብለዋል።

አክለዉም ጉዳዩን በተመለከተ ከደቡብ አፍሪካ እና ሌሎች አገሮች ጋር በመሆን በአፍሪካ ላይ የሚደርሰውን ኢፍትሃዊ ዉክልና ለማስቆም ትግላችንን እንቀጥላለን ብለዋል።

የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ በበኩላቸዉ ÷ፍትህ እንፈልጋለን፣ አፍሪካ በደንብ እንድትወከል እና እንድትደመጥ እንፈልጋለን፣ ምክንያቱም የ 1ነጥብ 3 ቢሊየን ህዝብ አመለካከት እና አስተሳሰብ በፀጥታዉ ምክር ቤት መደመጥ አልቻልም ፤ ይህ ግልፅ አግላይነት ሊቆም ይገባል ብለዋል፡፡

ይህን አህጉራዊ የፍትሃዊነት እንቅስቃሴ በግልጽ መቀላቀላቸውን ትናንት በትዊተር ገጻቸው ያስታወቁት የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ፥ አፍሪካን በተመለከተ በፀጥታው ምክር ቤት የሚወሰኑ ውሳኔዎች ከአፍሪካ ውክል እና ድምፅ ውጭ መተላለፍ እንደሌለባቸው አስምረውበታል።

በሚኪያስ አየለ

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.