Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያና የዩክሬን ቢዝነስ ፎረም ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 1፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያና የዩክሬን ቢዝነስ ፎረም በበይነ መረብ ተካሂዷል።
በጀርመንና ዩክሬን የኢትዮጵያ አምባሳደር ሙሉ ሰለሞን ኢትዮጵያ የቡና ፣ የአበባ ፣ የጥራጥሬ ፣ የዘይት እንዲሁም የቆዳ እና የቆዳ ውጤቶች ወደ ዩክሬን የመላክ እምቅ አቅም እንዳላት ገልፀዋል።
በፎረሙ ላይ በግብርና እና ግብርና ማቀነባበር፣ በመድኃኒት ፣ በትራንስፖርት እና በሎጂስቲክስ ዘርፎች የሚሰሩ 13 ዩክሬን ኩባንያዎች ምርታቸውን አሳይተዋል።
በኢትዮጵያ እና በዩክሬን መካከል የዲፕሎማሲ ግንኙነት በፈረንጆቹ 1905 የተጀመረ ሲሆን÷ በሁለቱ ሃገራት መካከል ያለው የንግድ ልውውጥ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱም ይነገራል።
በፎረሙ ላይ የሃገራቲ ዲፕሎማቶች እና ከ27 በላይ የዩክሬን ኩባንያ ተወካዮች መሳተፋቸውን በጀርመን የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመላክታል።
በተያየዘ ዜናም የኢትዮ-ኮርያ የንግድ አውደ ርዕይ በበይነ መረብ ተካሂዷል።
በዚህም የኢትዮጵያ መንግስት ከኮሪያ ጋር ያለውን የንግድ ግንኙነት ለማጠናከር በቁርጠኝነት እንደሚሰራ ተገልጿል።
በዚሁ ወቅት በኮሪያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሺፈራው ሽጉጤ ባደረጉት ንግግር÷ ኮቪድ -19 ባሳደረው ተጽዕኖ በርካታ የዓለም ሀገራት ዝቅተኛ የሆነ እድገት ሲያስመዘግቡ ኢትዮጵያ ግን ተጽዕኖውን ተቋቁማ እድገት ያስመዘገበች ሀገር መሆኗን ገልጸዋል።
የንግድና ኢንዱስትሪ ሚንስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አረጋ በበኩላቸው÷ኢትዮጵያና ኮሪያ ጠንካራ የዲፕሎማቲክና የኢኮኖሚ ግንኙነት ያላቸው ሀገሮች መሆናቸውን ገልፀዋል።
በፎረሙ ላይ ከ67 በላይ ታዳሚዎች የተሳተፉ ሲሆኑ ከእነዚህ ውስጥ 33ቱ የኮሪያ ኩባንያዎች መሆናቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.