ኤልሳልቫዶር ኤምባሲዋን በአዲስ አበባ ልትከፍት ነው
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኤልሳልቫዶር በአፍሪካ ሁለተኛ ኤምባሲዋን በአዲስ አበባ ለመክፈት መወሰኗን የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
በኤልሳልቫዶር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኤሌክሳንድራ ሂል ቲኖኮ የተመራ ልዑክ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀሥላሴ ጋር ተወያይቷል፡፡
በውይይታቸውም የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ለማጎልበት እንዲሁም በደቡብ ደቡብ ማዕቀፍ በባለብዙ መድረኮች ትብብራቸውን በማጠናከር ማስቀጠል በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡
ኤልሳልቫዶር በአፍሪካ ሁለተኛ ኤምባሲዋን በአዲስ አበባ ለመክፈት መወሰኗን የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የገለጹ ሲሆን÷ ለዚህ ሥራም የኢትዮጵያ መንግስት ድጋፍ እንደማይለያቸው አምባሳደር ታዬ አረጋግጠዋል፡፡
ሀገራቱ በቀጣይ የፖለቲካ ምክክሮች ለማድረግ በሚያስችሉ በትምህርት፣ ግብርና፣ ስፖርትና በተለያዩ ዘርፎች ትብብራቸውን ለማጠናከር መስማማታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡