Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት “የሱዳን ምርኮኞችን በአደባባይ ገድሏል” በሚል የሱዳን ጦር የሚያናፍሰው መረጃ መሰረተ ቢስ መሆኑን የመከላከያ ሚኒስቴር ገለፀ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 21 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት “የምርኮኛ አያያዝን ባልተከተለ መንገድ ወታደሮቼን ገድሏል” በሚል የሱዳን ጦር የሚያናፍሰው መረጃ መሰረተ ቢስ መሆኑን የመከላከያ ሚኒስቴር ገለፀ።
በጉዳዩ ላይ የሚኒስቴሩ የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮሎኔል ጌትነት አዳነ መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫቸውም በቅርቡ የሱዳን ወታደራዊ ሀይል ከአሸባሪው ህወሃት እና ሰራዊቱን በተለያዩ ጊዜ ከከዱ አመራርና አባላት ጋር ተቀናጅተው የኢትዮጵያን ድንበር አልፈው ሰርገው በመግባት በአካባቢው ሚሊሻና ነዋሪ ላይ ጥቃት መፈጸማቸውን ተናግረዋል።
ነገር ግን የኢፌደሪ መከላከያ ሰራዊት በአካባቢው ባልነበረበት ሁኔታ “ምርኮኞችን ገደለ” በሚል ከሱዳን በኩል ክስ መቅረቡ ፍፁም ተቀባይነት እንደሌለው ነው ያመለከቱት።
በአካባቢው ያልነበረው የኢፌዴሪ የመከላከያ ሰራዊት ምርኮኞችን ቢይዝ እንኳ መለያ ባህሪያቱ በሆኑት ህግ አክባሪነት እና ህዝባዊነት መሰረት ይይዛቸው እንደነበር ነው ያረጋገጡት።
የኢፌዴሪ የመከላከያ ሰራዊት መንግስት እርምጃ እንዲወሰድ ካዘዘው እንደ ሽፍታ ሳይሆን እንደመደበኛና ዘመናዊ ጦር በጥብቅ የዕዝ ሰንሰለት እየተመራ የሚንቀሳቀስ መሆኑን ተናግረዋል።
ለዘላቂ ሰላም ሲባልም የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት በቅርቡ የተከሰተውን ጉዳይ ለማጣራትና ለመመርመር የሚፈልግ አካል ካለ ለመተባበር እንዲሁም ከሁለቱ ሀገራት የተውጣጣ የመከላከያ ኮሚቴ እንዲያየው ከተፈለገም አብሮ ለመስራት ዝግጁ መሆኑንም አስታውቀዋል።
በታሪኩ ለገሰ
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.