Fana: At a Speed of Life!

አዘርባጃን ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የትብብር መስኮች ለማሳደግ ትኩረት ሰጥታ እንደምትሰራ ገለጸች

አዲስ አበባ፣ ህዳር 16፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) የኢትዮጵያ እና የአዘርባጃን አጋርነት ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነትን ባከበረ መልኩ መሆኑን በኢትዮጵያ የአገሪቱ ተጠባበቂ አምባሳደር ሩስላን ናሲቦቭ ገለጹ።

አምባሳደር ሩስላን ናሲቦቭ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ ÷ ኢትዮጵያና አዘርባጃን የጋራ ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነትን ያከበረ የአጋርነት ግንኙነት አላቸው ብለዋል።

ያም ብቻ ሳይሆን በአንድ አገር የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ አለመግባት የሚለውን ዓለም አቀፍ የአገራት ግንኙነት መርህንም ከግምት ያስገባ ግንኙነት መሆኑን ጠቁመዋል።

አዘርባጃን ኢትዮጵያ መሥራች የሆነችበትን ዓለም አቀፍ የገለልተኛ አገራት ንቅናቄ የወቅቱ ሊቀ መንበር መሆኗን አንስተው ÷ አገራቸው በዚህኛው ሚናቸው እነዚህን መርሆዎች እንደሚያጠናክሩ ገልጸዋል።

በሁለቱ አገራት መካከል በዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ ያለው አጋርነትም የተጠናከረ መሆኑን ገልጸው ÷ ኢትዮጵያ ለአዘርባጃን ለሠጠችው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።

ዓለም አቀፍ የዜና አውታሮች አዘርባጃንን በተመለከተ በተለያዩ ጊዜያት ሐሰተኛ መረጃዎች ማሰራጨታቸውን ጠቁመው ÷ ይህንንም ዜጎቿ በጋራ ቆመው ማለፋቸውን ተናግረዋል።

አዘርባጃንና ኢትዮጵያ ለበርካታ ዓመታት የዘለቀ ግንኙነት እንዳላቸው ጠቁመው ይህንንም በተለያዩ የትብብር መስኮች ለማሳደግ ትኩረት መሠጠቱን ገልጸዋል።

የአዘርባጃንና የኢትዮጵያ የሁለትዮሽ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተጀመረው እንደ አውሮፓዊያኑ ዘመን አቆጣጠር በ1992 ነው።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.