Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ከ20 እና 17 ዓመት በታች የሴቶች ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኞች ይፋ ሆኑ

የአሰልጣኞቹ ምርጫ እና ምደባ በእግር ኳስ ልማት ምክትል ፅህፈት ቤት ኃላፊ፣ በሴቶች እግር ኳስ ልማት፣ በውድድር ቋሚ ኮሚቴ እና የቴክኒክ ዳይሬክቶሬት አማካኝነት ነው የተካሄደው።

በዚህም የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች የሴቶች ብሄራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ፍሬው ኃይለገብርኤል እንዲሁም ምክትል አሰልጣኝ ህይወት አረፋይኔ ሆነው ተመርጠዋል፡፡

እንዲሁም ለኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች የሴቶች ብሄራዊ ቡድን ሳሙዔል አበራ ዋና አሰልጣኝ እንዲሁም ሰርክአዲስ እውነቱ ምክትል አሰልጣኝ በመሆን መመረጣቸውን ከፌዴሬሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.