Fana: At a Speed of Life!

የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል ተከበረ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 29፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በመላው ሀገሪቱ የክርስትና ዕምነት ተከታዮች ዘንድ ተከብሯል።
በዓሉን በማስመልከት የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፥ ጠቅላይ ሚነስትር ዐቢይ አሕመድ ፥ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፥ የሀይማኖት አባቶች እና የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች፣ የተለያዩ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
በመልዕክታቸውም በዓሉን በፍቅር፣ በሰላምና በመተሳሰብ ፥ ኮቪድን በመከላከል እንዲከበር ጥሪ አቅርበዋል።
በዓሉ በተለይም በቅዱስ ላልይበላ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ክርስትና የእምነት ተከታዮች፣ የተለያዩ ሃገራት ጎብኝዎች በተገኙበት በደመቀ ሃይማኖታዊ ስርዓት ነው የተከበረው፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.