Fana: At a Speed of Life!

የኦሮሚያ ክልል እና የጉራጌ ዞን ቴክኒክና ሙያ መምሪያ ለመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ አስረከቡ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልል እና የጉራጌ ዞን ቴክኒክና ሙያ መምሪያ ለመከላከያ ሰራዊት ከ27 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አድርገዋል፡፡
የኦሮሚያ ክልል የድጋፍ ሃብት አሰባሳቢ ኮሚቴ ሰብሳቢ ብርሀኑ ፈይሳ፥ የኦሮሚያ ክልል ከምስራቅ ሐረርጌ፣ ከባሌና ከአርሲ ዞን 423 ሰንጋዎችን እና 130 በጎችን ድጋፍ አድርጓል ብለዋል፡፡
“ሁልጊዜም ለጀግኖቻችን የማይታጠፈው የድጋፍ እጃችን ኢትዮጵያ ታሸንፍ ዘንድ በሃብትና በጉልበት የምንችለውን ሁሉ ስናደርግ ቆይተናል፤ ወደፊትም ከኢትዮጵያ ጎን እንቆማለን” ብለዋል፡፡
የጉራጌ ዞን ቴክኒክ እና ሙያ መምሪያ በስሩ የሚገኙትን 11 የመንግስት ኮሌጆች በማስተባበር 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ግምት ያላቸው 70 ኩንታል በሶ፣ 10 ኩንታል ቆሎ፣ 456 ኪሎ ግራም ቴምር ድጋፍ አድርጓል፡፡
የመምሪያው ሃላፊ ፈቱ አብዶ ሀገራችን ለህልውናዋ ስትል ተገዳ የገባችበትን ጦርነት በመደገፍ እስካሁን ድረስ በአጠቃላይ 146 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርገናል ማለታቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
የመከላከያ ፋይናንስ ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ማርታ ሉዊጂ ለተደረገው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል ፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.