Fana: At a Speed of Life!

የከተማ ግብርና የሙከራ ፕሮጀክት ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 16፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በፕላንና ልማት ሚኒስቴርና ፋርም አፍሪካ በተሰኘው ዓለም አቀፍ ድርጅት አማካኝነት በሙከራ ደረጃ የተከናወነው የከተማ ግብርና ፕሮጀክት ዛሬ ይፋ ተደርጓል።
በቢሾፍቱ ከተማ በተከናወነው ስነስርዓት ላይም የፕላንና ልማት፣ የከተማ ልማትና መሰረተ ልማት እንዲሁም የግብርና ሚኒስቴር ሚኒስትሮች የተገኙ ሲሆን ፕሮጀክቱን የተመለከቱ ገለፃዎችም ተደርገዋል።
በዚሁ ስነስርዓት ላይ የከተሞችን የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ ከፍተኛ ሚና ባለው የከተማ ግብርና ላይ በትኩረትና በቅንጅት መስራት እንደሚያስፈልግ ተመልክቷል።
የፕላንና ልማት ሚኒስቴር በተነሳሽነት የጀመረውና ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን 100 የህብረተሰብ ክፍሎችን ያቀፈው ይህ ፕሮጀክት የተቋማትን ተሳትፎ በማጠናከር በዘላቂነት ሊከናወን እንደሚገባም ተገልጿል።
የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትሯ ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ በበኩላቸው የከተማ ግብርና በከተሞች ያለውን ስር የሰደደ ችግር በማቃለልና የምግብ ዋስትናን በማረጋገጥ በኩል ሚናው ከፍተኛ ነው ብለዋል።
ተቋማትም ይህንን ተሞክሮ በመውሰድና ዙሪያቸውን በመቃኘት ሊሰሯቸው የሚገቡ በርካታ ተግባራት አሉ ያሉት ሚኒስትሯ፥ ሚኒስቴር መስሪያ ቤታቸውም በጅምር የታየውን ተሞክሮ ለማስፋፋት ይሰራል ብለዋል።
በዛሬው ዕለት ይፋ የተደረገውን የሙከራ ፕሮጀክት ዘላቂ በማድረግ ለማስፋፋት ሶስቱም የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች በቅንጅት ለመስራት የሚያስችል ስምምነት ላይ መድረሳቸውን የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።
የፕሮጀክቱ ፅንሰ-ሀሳብም የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከመነሻው ጀምሮ የሚያውቁት እና ከፍተኛ ትኩረት የሰጡት መሆኑን ገልጸው፤ ፕሮጀክቱ የሚኖረውን የአንድ አመት ከሶስት ወር የሙከራ ምዕራፍ ትግበራ እንደተጠናቀቀ፥ ከሚገኙት ተሞክሮዎች በመነሳት በመላው አዲስ አበባ ላይ በሚገኙ ሌሎች ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ተስፋፍቶ ተግባራዊ እንደሚደረግ ፕሮግራም የተያዘለት መሆኑንም የፕላን ሚኒስትሯ ዶ/ር ፍጹም አሰፋ ጠቁመዋል።
ፕሮጀክቱ ከምግብ ዋስትና አንፃር የምግብ አቅርቦትን የሚጨምር፣ የስራ ዕድልን የሚፈጥርና ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እንዲሁም በየአካባቢው ባሉ ወረዳዎችን ተጠቃሚ ያደርጋል ብለዋል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.