Fana: At a Speed of Life!

የኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፓርክን በአፋጣኝ ወደ ስራ ለማስገባት አስፈላጊው ርብርብ ይደረጋል-አቶ ሳንዶካን

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሳንዶካን ደበበ የተመራው የአመራሮችና የሰራተኞች ልዑክ በአሸባሪው የህወሓት ዘራፊ ቡድን ዝርፊያና ውድመት የደረሰበትን የኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፓርክ ጎብኝቷል።
 
በጉብኝቱ የልዑክ ቡድኑ የፓርኩን የአንድ ማዕከል አገልግሎት፣ የማምረቻ ሼዶች፣ የኬሚካል ማጣሪያ እና ሌሎች በፓርኩ ውስጥ አገልግሎት ይሰጡ የነበሩና በሽብር ቡድኑ ህወሓት ዝርፊያና ውድመት የደረሰባቸውን ቦታዎች ተመልክቷል።
 
በዚህም የፓርኩ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የቢሮ እቃዎችና የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሲስተሞች፣ የአምራች ኩባንያዎች ቢሮዎችና ቁሳቁሶች፣ ለውጭ ገበያ የተዘጋጁ የጨርቃ ጨርቅ አልባሳትና የቆዳ ውጤቶች፣ የምርት ማከማቻ መጋዘኖች፣ ለምርት የተዘጋጁ ጥሬ እቃዎች፣ የተለያዩ ተሽከርካሪዎች እንዲሁም ሌሎች በፓርኩ ውስጥ የሚገኙ ቁሳቁሶች ዝርፊያና ውድመት እንደደረሰባቸው ታውቋል።
 
ከጉብኝቱ በተጨማሪም የፓርኩ ስራ አስኪያጅን ጨምሮ በፓርኩ ውስጥ ይሰሩ የነበሩ ባለሃብቶችና የተለያዩ ድርጅቶች ስራ አስኪያጆች ከኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሳንዶካን ደበበ ጋር ተወያይተዋል።
 
በውይይቱም የደረሱ ጉዳቶችን ማጣራትና የጉዳት መጠኑን ማወቅ እንዲሁም በአፋጣኝ ወደ ስራ መግባት የሚቻልባቸው አማራጮችን መመልከት የሚሉ ነጥቦች ተነስተዋል።
 
በአሸባሪ ቡድኑ የደረሰው ዝርፊያና ውድመት አሳፋሪና እጅግ አሳዛኝ ነው ያሉት ስራ አስፈፃሚው፥ ይህም የሽብር ቡድኑ ለሀገር እድገት ጸር መሆኑን በግልጽ ያሳየበት ተግባር ነው ብለዋል።
 
ፓርኩን በአፋጣኝ ወደ ስራ ለማስገባት ግብረ ኃይል ተቋቁሞ አስፈላጊው ርብርብ እንደሚደረግም ነው አቶ ሳንዶካን የተናገሩት።
 
አምራች ድርጅቶቹና ሃላፊዎቻቸው በበኩላቸው በፓርኩና ንብረቶች ላይ በደረሰው ጉዳት እጅግ እንዳሳዘናቸው መግለጻቸውን ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.