Fana: At a Speed of Life!

የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ የ405 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ የ405 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ማድረጉ ተገለፀ፡፡

ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አሕመድ ሽዴና የዓለም ባንክ ግሩፕ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ኦስማን ዲዮን ተፈራርመዋል፡፡

የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ ካደረገው የ405 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ዉስጥ 195 ሚሊየን ድጋፍ ስምምነቱ በኢትዮጵያ ውስጥ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ የሚያስከተለውን ጉዳት ለመቀነስ እና በሽታውን በመከላከል ሂደት ውስጥ ውጤታማ የኮቪድ 19 ክትባትን ለማከናወን እንዲያስችል ነው ተብሏል ።

ከቀናት በፊት የተፈፀመው ቀሪው የ210 ሚሊየን ዶላር የድጋፍ ስምምነት ቆላማ በሆኑ አካባቢዎች የከርሰ ምድር ውሃን ለማልማትና ጥቅም ላይ ለማዋል የሚያስችል ስምምነት መሆኑን የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አሕመድ ሽዴ ተናግረዋል ።

በፀጋዬ ወንድወሰን

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.