Fana: At a Speed of Life!

የደረሱ ሰብሎች እየተሰበሰቡ ነው- የደቡብ ክልል ግብርና ቢሮ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 17 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰሜን የሀገሪቱ አካባቢዎች እየተካሄደ ያለውን የህልውና ዘመቻ ተከትሎ የምርት እጥረት እንዳይከሰት ቢሮው የክልሉ አርሶ አደሮችን በማስተባበር ከብክነት የፀዳ ምርት የመሰብሰብ ስራ እያከናወነ ነው፡፡

በሰሜን አንድም ጥይት አትመክንም ከምርት አንድም ፍሬ አትባክንም’ በሚል ንቅናቄ ነው የደረሰ ሰብል እየተሰበሰበ የሚገኘው፡፡

በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ክላስተር አስተባባሪና የግብርና ቢሮ ሀላፊ አቶ ኡስማን ሱሩር፥በክልሉ የመኸር ሰብል በደረሰባቸው አካባቢዎች አብዛኛው ምርት መሠብሠቡን ገልፀዋል።

ግጭት ባለባቸው አማራ፣ አፋርና ትግራይ ክልል አርሶ አደሮች የግብርና ስራዎችን እንደ ከዚህ ቀደሙ ባለማከናወናቸው በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ሊፈጠር የሚችለውን ጫና ለማስቀረት እየተሰራ ይገኛል።

በእርዳታ ስንዴ ሰበብ የሚመጣን ጫና ለማስቀረት’ ቁጭት’ የሚል ስያሜ የተሰጠው የግብርና ልማት ስራም በክልሉ መጀመሩን ነው አቶ ኡስማን የተናገሩት።

ከጦር ግንባር ጎን ለጎን በልማት ስራ ድል መምታት እንዲቻል አርሶ አደሮች የግብር ዘርፍ ጀነራሎች በመሆናቸው ከመቼው ጊዜ በበለጠ ለሀገራቸው ደጀን ሊሆኑ እንደሚገባ ጥሪ አቅርበዋል።

በክልሉ በበጀት አመቱ በበጋ መስኖ 15 ሺህ ሄክታር መሬት በማልማት 500 ሺህ ኩንታል ምርት ለመሠብሠብ ታቅዷል።

በሞሊቶ ኤልያስ

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.