Fana: At a Speed of Life!

የድምፅ መስጫ ወረቀት የህትመት ቅደም ተከተል ሎተሪ ስነ-ስርዓት ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 2 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)  የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የድምፅ መስጫ ወረቀት ቅደም ተከተል ሎተሪ የማውጣት ስነስርዓት ተካሂዷል፡፡

በ6ኛው አጠቃላይ ምርጫ ላይ እንዲወዳደሩ ህጋዊ ዕውቅና የተሰጣቸው የፖለቲካ ፓርቲዎች የድምፅ መስጫ ወረቀት ቅደም ተከተል በዕጣ ተለይቶ ይፋ ተደርጓል፡

በዚህ ሂደትም በሁሉም የምርጫ ክልሎች ያሉ ተፎካካሪዎች ዕጣ የማውጣት ስነስርዓት  ተከናውኗል  ።

ለተከታታይ 4 ቀናት የሁሉንም የምርጫ ክልሎች የዕጣ ማውጣት ስነ-ስርዓት ሲካሄድ የቆየ ሲሆን÷ በዛሬው ዕለትም የማጠቃለያ ፕሮግራም  ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች በተገኙበት  ተከናውኗል ።

በሀገሪቱ  የምርጫ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የተከናወነው የድምፅ መስጫ ወረቀት የህትመት ቅደም ተከተል ዕጣ የማውጣት ስነ- ስርዓት÷  ለምርጫው ዲሞክራሲያዊነት እና ግልጽነት መስፈን አንዱ ማሳያ መሆኑን በዕጣ ማውጣት ስነስርዓት ላይ የተገኙ የፖለቲካ ፖርቲ ተወካዮች ገልጸዋል ።

በወቅቱም የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሀላፊ ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ÷ ምርጫ የምናካሂደው ለሀገር ሉዓላዊነትና ለዜግነት ክብር በመሆኑ ሁሉም ተፎካካሪዎች የምርጫ ህጉን አክብረው መሳተፍ አለባቸው ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ምርጫው  ሰላማዊ፣ዴሞክራሲያዊ ፣ ግልፅነት የሰፈነበትና አሳታፊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የተሰጣቸውን ሀላፊነት ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸው የብልፅግና ፓርቲን  በመወከል በዕጣ ማውጣት ስነስርዓቱ ላይ የተሳተፉት  ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ መናገራቸውን  ከከተማ አስተዳደሩ ፕሬስ ሰክሬተሪያት ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.