Fana: At a Speed of Life!

የጃፓኑ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ በተፈጸመባቸው ጥቃት ህይወታቸው አለፈ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 1 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጃፓኑ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ በተፈጸመባቸው ጥቃት ህይወታቸው አለፈ።

ሺንዞ አቤ በናራ ከተማ በዕጩ ቅስቀሳ ወቅት ከኋላቸው በጥይት ተመተው ሆስፒታል መግባታቸው ይታወሳል።

በሆስፒታል ጥብቅ የህክምነናክትትል ቢደረግላቸውም መትረፍ አለመቻላቸውን ቢቢሲ እና ሲ ጂ ቲ ኤን ዘግበዋል።

ጥቃቱን በማድረስ የተጠረጠረው ግለሰብም ከእነ መሳሪያው በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተደረገ መሆኑ ተገልጿል።

የ67 አመቱ ሺንዞ አቤ ጃፓንን ለበርካታ አመታት በጠቅላይ ሚኒስትርነት መምራታቸው ይታወሳል።

ሺንዞ አቤ ከጤና እክል ጋር በተያያዘ በፈረንጆቹ 2020 ነበር ስልጣናቸውን በፈቃዳቸው የለቀቁት።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.