Fana: At a Speed of Life!

የግሸን ደብረ ከርቤ ዓመታዊ ክብረ በዓል በድምቀት እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣መስከረም21፣2014 (ኤፍ ቢሲ) የግሸን ደብረ ከርቤ ዓመታዊ ክብረ በዓል በተለያዩ ሃይማኖታዊ ሥነ ሥርዓቶች እየተከበረ ነው፡፡
አሚኮ እንደዘገበው የሃይማኖቱ ተከታዮች በዓሉ አስተማማኝ በሆነ የሰላም ሁኔታ እየተከበረ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
ከተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የተገኙ ምዕመናን፥ በዓሉን ሃይማኖታዊ ሥርዓቱን በጠበቀ መልኩ እያከበረ መሆኑን  ነው የተናገሩት፡፡
በክብረ በዓሉ ላይ ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የታደሙ የሃይማኖት አባቶች እና የሃይማኖቱ ተከታዮች ተገኝተዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.