Fana: At a Speed of Life!

ዩኒሴፍ ለተፈናቃዮች ከ30 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጣ ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 25 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የተመድ ህጻናት መርጃ ድርጅት (ዩኒሴፍ) በአሸባሪው ህወሓት ወረራ ምክንያት ችግር ለደረሰባቸው እና ለተፈናቀሉ ዜጎች ከ30 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ የተለያዩ ቁሳቁሶችን አበረከተ።
 
ድጋፉን የተረከቡት የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገር ዩኒሴፍ ለአማራ ክልል ለችግር ጊዜ ደራሽ በመሆኑ አመስግነዋል።
 
በቀጣይም ድርጅቱ ድጋፉን እንዲቀጥልና ሌሎች የሰብዓዊ ድጋፍ ድርጅቶች ተመሳሳይ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።
 
ለተማሪዎች ደብተር እና እስኪርቢቶ፣ የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁስ እንዲሁም ፍራሾች እና ሌሎች ቁሳቁስ ነው ዩኒሴፍ ድጋፍ ያደረገው።
 
የዩኒሴፍ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር አዴል ኮድር፥በሰሜን ጎንደርና አካባቢው ጉብኝት ማድረጋቸውን ገልፀው በርካታ ህፃናት በምግብ እጥረት ፈታኝ ሁኔታ ውስጥ ናቸው ማለታቸውን ኢቢሲ ዘግቧል።
 
ታዳጊዎች በመጭው የትምህርት ዘመን በትምህርት ገበታ ለመታደም አሳሳቢ ሁኔታ መኖሩንም ጠቁመዋል።
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.