Fana: At a Speed of Life!

ዳያስፖራው በህጋዊ መልኩ ገንዘብ በመላክ ድጋፉን እንዲቀጥል ተጠየቀ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 13፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ገንዘብ በህጋዊ መንገድ ወደ አገር ቤት እንዲያስተላልፉ ጥሪ አቀረበ፡፡

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዲኤታ ሰላማዊት ካሳ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

በመግለጫቸውም በመላው ዓለም የሚገኙ ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች በውጭ ሃገራት በሚገኙ የተለያዩ ከተሞች የድጋፍ ሰልፍ ማድረጋቸውን አንስተዋል።

ሰልፎቹ ኢትዮጵያ ለተቀረው ዓለም ድምጿንና እውነታዋን ያሳየችበት፣ ለተመረጠው መንግስት ድጋፉን የገለፀችበት ነውም ብለዋል።

ኢትዮጵያውያኑ ዞሮ መግቢያቸው የሆነችዋን አገር ለማፍረስ የተንቀሳቀሱ አካላት ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ መልዕክት አስተላልፈዋልም ነው ያሉት ሚኒስትር ዲኤታዋ፡፡

ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን አገራቸውን በተለያዩ መንገዶች ለመደገፍ በትዕይንተ ህዝቦቹ ቃል መግባታቸውንም አንስተዋል፡፡

በውጭ የሚኖሩ ወገኖች በህጋዊ መልኩ ገንዘብን በማስተላለፍና በቀጥተኛ መልኩ የጀመሩትን ድጋፍ ሊቀጥሉ ይገባል ነው ያሉት፡፡

መንግስትም ኢትዮጵያውያኑ የሚሳተፉባቸውን መንገዶች ያመቻቻል ብለዋል፡፡

በአፈወርቅ እያዩና በርናባስ ተስፋዬ

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.