Fana: At a Speed of Life!

ግሪክ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ግንኙነት ይብልጥ ለማጠናከር ፍላጎት እንዳላት ገለጸች

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 10፣2014(ኤፍ ቢሲ) ተቀማጭነታቸው በሮም፣ ጣሊያን ሆኖ በግሪክ የኢትዮጵያ አምባሳደር ደሚቱ ሀምቢሳ ከግሪክ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የፖለቲካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጀኔራል ሀሪስ ላላኮስ ጋር ተወያዩ።
 
በውይይቱ አምባሳደር ደሚቱ ስለ የህወሓት የሽብር ቡድን የአገሪቷን ሰላም ለማደፍረስና አንድነቷን ለማናጋት ስለሰራቸው የጥፋት ስራዎች፣ የሽብር ቡድኑ የመከላከያ ሰራዊት ሰሜን እዝ ከማጥቃት አንስቶ በአጎራባች ክልሎች ያደረሳቸውን ጥፋቶች እንዲሁም በመንግስት በኩል ስለተወሰዱ እርምጃዎች ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
 
በሌላ በኩል ምዕራባውያን የውሸት ፕሮፖጋንዳ በማሰራጨት የተለያዩ ጫናዎችን ለማሳረፍና እርምጃዎችን ለመውሰድ ስለተደረጉ እንቅስቃሴዎች እንዲሁም እ.ኤ.አ. ታህሣሥ 17 ቀን 2021 በሰብአዊ መብቶች ካውንስል የተደረገው ስብሰባ አግባብነት የሌለው ስለመሆኑ በጥልቀት አስረድተዋል።
 
በኢትዮጵያና በግሪክ መካከል ለረጅም ጊዜ የቆየውን ግንኙነት ለማጠናከር ማለትም በፖለቲካ፣ በቢዝነስና በቱሪዝም መስኮች በጋራ ለመስራት በኢትዮጵያ በኩል ፍላጎት እንዳለ ገልጸዋል።
 
ሀሪስ ላላኮስ በበኩላቸው÷በግሪክና በኢትየጵያ መካከል ያለውን ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር በአገራቸው በኩል ፍላጎት እንዳለ ተናግረዋል፡፡
 
በተለይም በአሁኑ ሰአት ግሪክ ከአፍሪካ አገራት ጋር ያላትን ግንኑነት ለማጠናከር እየሰራች እንደሆነና ኢትዮጵያ ደግሞ የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ እንደመሆኗ ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር መስራት እንደሚፈልጉ መግለፃቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.