Fana: At a Speed of Life!

ግብርናን ለማሳደግ የሚያግዝ የወጣቶች የፈጠራ ውድድር በይፋ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ዕድሜያቸው ከ18-29 የሆኑ እና በኢትዮጵያ ግብርናን ለማሻሻል የሚረዳ የፈጠራ ሀሳብ ያላቸው ዜጎችን የሚያሳትፍ ውድድር በይፋ ተጀምሯል::

“አዩቴ ኢትዮጵያ ቻሌንጅ” የተሰኘው ይህ ውድድር÷በ ሄይፈር ኢንተርናሽናል የተዘጋጀ ሲሆን  የግብርና ቴክኖሎጂ ፈጠራ ላይ ያተኮረ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

ውድድሩ ፌር ኤንድ ሰስተነብል ኢትዮጵያ ከተለያዩ የመንግስት አካላት፣ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትና የፋይናንስ ተቋማት ጋር በመተባበር እንደሚመራው ተገልጿል፡፡

የውድድሩ አላማ በኢትዮጵያ ያሉ አነስተኛ አርሶ አደሮችን ተግዳሮቶች መቅረፍ ምርትን ምርታማነትን፣ ገቢን፣ የፋይናንስ አቅርቦትንና የመቋቋም አቅም ያላቸውን የግብርና ቴክኖሎጂ ሀሳቦችን አወዳድሮ መሸለም እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡

አዩቴ ቻሌንጅ ከአንድ እስከ ሶስት ለሚወጡ አሸናፊዎች 20 ሺ ዶላር ሽልማት ማዘጋጀቱም ነው የተገለጸው፡፡

የማመልከቻ ጊዜውም ከግንቦት 13 ቀን 2014 ጀምሮ ለተከታታይ ሰባት ቀናት የሚቆይ ሲሆን÷ወጣት የፈጠራ ባለሙያዎች ለውድድሩ ማመልከት የሚችሉት የኦንላይን የማመልከቻ ፎርሙን በመሙላት ብቻ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

የማመልከቻ ፎርሙን ለማግኘትም  የሚከተለውን  ሊንክን በመጫን  ማግኘት ይቻላል :- https://ayute-ethiopia.et/apply-here/

 

በዘቢብ ተክላይ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.