Fana: At a Speed of Life!

ግብፅ እና ሱዳን የአፍሪካ ህብረት የተሰጠውን ሃላፊነት የሚያንኳስስ ሙከራ ማድረጋቸው ተቀባይነት የለውም – ኢንጂነር ስለሺ

ግብፅ እና ሱዳን የአፍሪካ ህብረት የተሰጠውን ሃላፊነት የሚያንኳስስ ሙከራ ማድረጋቸው ተቀባይነት የለውም – ዶ/ር ስለሺ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 29 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ግብፅ እና ሱዳን የአፍሪካ ህብረት የተሰጠውን ሃላፊነት የሚያንኳስስ ሙከራ ማድረጋቸው ተቀባይነት እንደሌለው የውሃ፣ መስኖና ኢነርጅ ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ገለጹ፡፡

ሚኒስትሩ በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ መዲና ኪንሻሳ ስለተደረገው የሶስቱ ሀገራት የውጭ ጉዳይና የውሃ ሚኒስትሮች ውይይት በሰጡት መግለጫ፥ ካይሮ እና ካርቱም ድርድሩን የማጓተት ስትራቴጂን በመከተላቸው ሰፊ ጊዜ ጠፍቷል ብለዋል።

ደቡብ አፍሪካ ከታዛቢነት እንድትወጣ የቀረበው ሀሳብም የአፍሪካ ህብረትን ክብር የማይመጥን ነው ሲሉ ተናግረዋል።

የሀገራቱ የድርድሩን ቅርጽ የመለወጥ እና ከይዘት ይልቅ ሂደት ላይ ማተኮር በኪንሻሳው ስብሰባ ላይ መታየቱንም ነው ሚኒስትሩ የጠቆሙት።

በመግለጫቸው ኢትዮጵያ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ በኩል ድርድሩ በፍጥነት እንዲጠናቀቅ የአባይን ውሃ ምክንያታዊ እና ፍትሃዊ በሆነ መንገድ የመጠቀም ሉዓላዊ መብቷን እንዳስረዳችም ገልጸዋል።

ከትብብር ይልቅ የአንድ ወገን ተጠቃሚነትን ለሚያረጋግጥ ሃሳብ ምንም አይነት ቦታ እንደሌላትም ሚኒስትሩ በመግለጫቸው ያነሱት።

ከግድቡ ውሃ ሙሌትም ይሁን ከአጠቃላይ የግድቡ ሁኔታ ጋር በተያያዘ ጠቃሚ መረጃዎችን ለመለዋወጥ ዝግጁነቷን በመጥቀስም፥ ሁለተኛው ዙር የውሃ ሙሌት በተያዘለት ጊዜ እንደሚካሄድ አስረድተዋል።

ከሱዳን በኩል እየተነሱ ያሉ ወቀሳዎችም ምንም አይነት መሰረት የሌላቸው መሆኑን በኪንሻሳው ስብሰባ በስፋት ማስረዳታቸውንም አውስተዋል።

ግብፅ ድጋፍ የቸረችው የሱዳን ድርድሩን የማጓተቻ ሀሳቦች ከታዛቢዎች ጋር የተያያዙ እና የድርድሩን ቅርጽ የመለወጥ እንቅስቃሴዎች ተቀባይነት የሌላቸው መሆኑንም ሚኒስትሩ ጠቅሰዋል።

ሃገራቱ የሚያደርጉት ቀጣዩ የሶስትዮሽ ድርድር የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ፕሬዚዳንት በሚሰጡት አቅጣጫ ይወሰናል ተብሏል፡፡

በፋሲካው ታደሰ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.