Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የቀድሞ የኢትዮጵያ መሪዎችን የጀግንነት ዓርማ አድሰዋል – ብ/ ጄኔራል ዋሲሁን ንጋቱ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የቀድሞ የኢትዮጵያ መሪዎችን የጀግንነት ዓርማ አድሰዋል ሲሉ የቀድሞ ጦር ጄኔራል ብርጋዴር ጄኔራል ዋሲሁን ንጋቱ ተናገሩ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በጦር ሜዳ በመገኘት ሠራዊቱን በመምራታቸው የምኒሊክንና የሌሎችን የኢትዮጵያ የቀድሞ መሪዎች የድል አድራጊነት ዓርማን ማደስ ችለዋል ብለዋል።

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ውሳኔያቸው አገርን ለማዳን የተደረገ ትልቅ እርምጃ ነው ያሉት ብርጋዴር ጄኔራል ዋሲሁን ንጋቱ ÷ የኢትዮጵያን መሪዎችን የአሸናፊነት ታሪክ ደግመዋል ሲሉ ገልጸዋል፡፡

አጼ ምኒልክ በመጀመሪያው የጣሊያን ወረራ ጊዜ ‹‹ስንቅህን በአህያ፤ አመልህን በጉያህ›› አድርገህ ተከተለኝ ብለው ነበር ወደ ግንባር ያመሩት፤ ሕዝቡም ጥሪውን ተቀብሎ ወራሪው ኃይል በአጭር ጊዜ እንዲመለስ አድርጓልም ነው ያሉት።

አሁንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወራሪውን ለማንበርከክ ወደ ግንባር መዝመታቸው አገርን ለማዳን የተደረገ ታሪካዊ ውሳኔ አድርጎ ማየት ይገባል ተብሏል።

የኢትዮጵያ ሕዝብ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር በመሰለፍ አገርን ለማፍረስ የሚንቀሳቀሱ ወራሪ ኃይሎችን መደምሰስ አለበት ሲሉ መልዕክት ማስተላለፋቸውን ኢፕድ ዘግቧል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.