Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ 2 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር ወጪ የሚደረግበትን የጅማ – ጭዳ አስፋልት መንገድ ግንባታን አስጀመሩ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 16 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የጅማ ጭዳ የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታን አስጀመሩ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የግንባታ ፕሮጀክቱን የመሰረት ድንጋይ ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን እንዲሁም ከካቢኔ አባላቶቻቸው ጋር በመሆን በኮንታ ልዩ ወረዳ ጭዳ ከተማ አስተዳደር አኖረዋል፡፡

80 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለውን የጅማ ጭዳ አስፋልት መንገድ ግንባታ የሚያከናውነው የቻይናው ቲ ሲ ጁ ሲቪል ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የተሰኘ ዓለም አቀፍ ተቋራጭ ነው፡፡

በአራት አመታት የግንባታ ጊዜ ውስጥ ይጠናቀቃል የተባለው የጅማ ጭዳ መንገድ ፕሮጀክት፥ 2 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር ወጪ ይደረግበታል ተብሏል፡፡

ወጪው የአፍሪካ ልማት ባንክ፣ የጃፓን ዓለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅት እና የኢትዮጵያ መንግሥት በጋራ የሚሸፈን ነው፡፡

የጅማ ጭዳ መንገድ አካባቢው ቡናና ፍራፍሬ አብቃይ በመሆኑ ምርቶችን ወደ ማዕከላዊ እና ዓለም አቀፍ ገበያ ለማቅረብ ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው፡፡

መንገዱ የኦሮሚያ እና ደቡብ ክልሎችን የሚያስተሳስር ሲሆን የጨበራ ጩርጩራ ብሔራዊ ፓርክን ለመጎብኘት እንዲሁም ከጊቤ 3 እና ጊቤ 4 የኮይሻ ኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫ ግድብ ስራ ጋር ተያያዥ ሚና እንደሚጫወት ተገልጿል፡፡

ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ የአዲስ አበባ-ጅማ-ቦንጋ-ሚዛን መንገድን ከሆሳዕና-ሶዶ-አርባምንጭ መንገድ ጋር የማገናኘት ተጨማሪ ሚና አለው፡፡

ይህም በቀጠናው የሚገኘውን ከፍተኛ የተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ ሃብት ለመጠቀም የሚያስችል ነው፡፡

በሶዶ ለማ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.