Fana: At a Speed of Life!

ጤና ሚኒስቴር በመጠለያ የሚገኙ ዜጎች የጤና ሁኔታ ላይ ምልከታ አካሄደ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሸባሪው የህውሓት ቡድን ለተጎዱ የጤና ተቋማትና በችግሩ የተፈናቀሉ ዜጎችን ጤንነት ለመጠበቅ የሚደረጉ ድጋፎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የጤና ሚኒስቴር ዴኤታ ዶክተር ደረጀ ዱጉማ ገለጹ፡፡
የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጀ ዱጉማ እና የሚኒስቴሩ የእናቶች እና ህጻናት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶክተር መሰረት ዘላለም ከኮንቦልቻ ከተማ ከንቲባ እና ከጤና መምሪያ የስራ ኃላፊዎች ጋር በመሆን በጊዜአዊ መጠለያ የሚገኙ ዜጎችን ጎብኝተዋል፡፡
ከዩ ኤን ኤፍ ፒኤ በድጋፍ የተገኙ 590ሺህ ዶላር ግምት ያላቸው የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁስ፣ የስነ ተዋልዶ ኪቶች እና የኮቪድ መከላከያ ግብዓቶችን በመጠለያ ለሚገኙ ወገኞች ማስረከብ ተችሏል፡፡
አሸባሪው ቡድን ባደረሰው ጥቃት በርካታ ዜጎች ከቤት ንብረታቸው በመፈናቀላቸው ለተለያዩ የጤና ጉዳቶች መጋለጠቸውን ጠቁመው÷ በዩ ኤን ኤፍ ፒ ኤ በኩል የተደረገው ድጋፍ በአስፈላጊ ወቅት እና አካባቢ የተደረገ ነው ሲሉ ዶክተር ደረጄ አመስግናዋል፡፡
የሚኒስቴሩ የእናቶችና ህጻናት ጤና አገልግሎት ዳይሬክተር ዶክተር መሰረት ዘላለም በበኩላቸው÷ ህውሓት ባደረሰው ጉዳት በርካታ ዜጎች ለጤና ጉዳት እየተጋለጡ ነው ብለዋል፡፡
በተለይ እናቶች፣ ህጻናትና ወጣቶች ለተለያዩ ጤና ጉዳቶች እየተዳረጉ መሆናቸውንም ገልጸዋል፡፡
በዚህ አስቸጋሪ ወቅት እርጉዝ እናቶች እና ህጻናት ለምግብ እጥረት ችግር እንዳይጋለጡ በጦርነት ወቅት ሊደረስ ከሚችል የተወሳሰበ የስነ ተዋልዶ ጤና ጉዳትም ለመከላከል የጤና ሚኒስቴር አጋር አካላትን በማሳተፍ በትኩረት እየሰራ መሆኑን አብራርተዋል፡፡
የ ዩ ኤን ኤፍ ኤ ካንትሪ ዳይሬክተር ዳኒያ ጋይለ እንደተናገሩት÷ ድርጅታቸው በጦርነት ወቅት ለልዩ ልዩ ጉዳቶች ይበልጥ ተጋላጭ የሆኑ ሴቶችን፣ ህጻናትን፣ እርጉዝ እናቶችና ወጣቶችን ከከፋ የጤና ጉዳት ለመጠበቅ የተለያዩ ፕሮግራሞችን ቀርጾ እየሰራ መሆኑን ተናገረው የተደረገው ድጋፍም የዚሁ የሰብዓዊ ድጋፍ ተግባር አካል ነው ብለዋል፡፡
በቀጣይም ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ማረጋገጣቸውን ከጠየና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.