Fana: At a Speed of Life!

ህዝቡን ከድህነት ለማላቀቅና የልማት ተጠቃሚ ለማድረግ በትኩረት ይሰራል- ጨፌ ኦሮሚያ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 21 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልል ህዝብን ከድህነት ለማላቀቅና የልማት ተጠቃሚ ለማድረግ በትኩረት እንደሚሰራ የጨፌ ኦሮሚያ አስታወቀ።
ሁለተኛ ቀኑን የያዘው የጨፌ ኦሮሚያ መደበኛ ጉባኤ ዛሬም ቀጥሏል።

ጨፌ ኦሮሚያ በ5ኛ የስራ ዘመን 6ኛ አመት 13ኛ መደበኛ ስብሰባው የ2013 ዓ.ም የግማሽ አመት የስራ አፈፃፀምን የገመገመ ሲሆን ዛሬ በሁለተኛ ቀን ውሎው የተለያዩ አዋጆች ላይ በመወያየት አጽድቋል።

የኦሮሚያ የቤቶች ልማት አስተዳደርና ማስተላለፍ፣ ኤክሳይዝ ታክስ፣ የውሀ ኃብት ልማት፣ የግብርና ምርት ጥራት ቁጥጥር፣ ስታቲስቲክስ፣ የመአድን ኃብት ልማት እና የክልሉን ጠቅላይ አቃቤ ህግ ለማሻሻል የተዘጋጁ ረቂቅ አዋጆችን መርምሮ አጽድቋል፡፡

ጉባኤው የተለያዩ ሹመቶችን መርምሮ ያፀድቃል ተብሎም ይጠበቃል፡፡

የክልሉን ህዝብ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ዋነኛ ትኩረታችን በመሆኑ በ10 አመት የክልሉ ስትራቴጂክ እቅድ ውስጥ ህዝቡን ከድህነት ማላቀቅ በቀዳሚነት ተይዟል ብሏል ጨፌው፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.