Fana: At a Speed of Life!

ለእግር ኳስ ፌዴሬሽን አመራርነት የመጨረሻ እጩዎች ይፋ ሆኑ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በምርጫ አስፈፃሚው ኮሚቴ ከታዩ በኋላ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የፕሬዚዳንት እና ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የመጨረሻ እጩዎች ይፋ ሆነዋል፡፡

በዚህም መሰረት 32 የፌዴሬሽኑ የስራ አስፈፃሚ አባለት ለመጨረሻ እጩነት ሲቀርቡ÷ 3 እጨዎች ደግሞ ለእግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንትነት የመጨረሻ እጩዎች በመሆን ቀርበዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የምርጫ ጠቅላላ ጉባኤ የቦታ ለውጥ እንዲደረግ መወሰኑን አስታውቋል፡፡

ፌዴሬሽኑ ጠቅላላ ጉባዔውን በጎንደር ከተማ ሊያካሂድ ቀጠሮ ይዞ የነበረ ቢሆንም÷ 14ኛው ጠቅላላ ጉባኤ እና የምርጫ ጠቅላላ ጉባኤ ቦታ እንዲቀየር የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ኢመርጀንሲ ኮሚቴ ውሳኔ ማሳለፉን ከፌዴሬሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.