Fana: At a Speed of Life!

ለገበታ ለሃገር ፕሮጀክት ከዳያስፖራው 283 ሺህ 378 የአሜሪካ ዶላር ተሰብስቧል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለገበታ ለሀገር ፕሮጀክት ዜጎች እያደረጉት ያለው ድጋፍ አስደናቂ መሆኑን አስታወቁ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፌስ ቡክ ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ እስካሁን ከዳያስፖራው 283 ሺህ 378 የአሜሪካ ዶላር መዋጣቱን አስታውቀዋል፡፡

ለዚህ ሀገራዊ ጥሪ ምላሽ ከሰጡ ትውልደ ኢትዮጵያውያን መካከል በዕጣ አሥር ዳያስፖራዎች በኅዳር አጋማሽ በሚካሄደው የገበታ ለሀገር መርሐ ግብር ላይ ሙሉ ወጪያቸው ተሸፍኖ ግብዣ ይደረግላቸዋል ብለዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለገበታ ለሃገር ያቀረቡትን ጥሪ ተከትሎ በርካታ ተቋማትና ድርጅቶች ድጋፍ እያደረጉ መሆኑ ይታወቃል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.