Fana: At a Speed of Life!

ሉሲዎቹ ደቡብ ሱዳንን 11 ለ0 አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 3፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ደቡብ ሱዳንን 11 ለ0 አሸንፏል፡፡

ትናንት ምሸት በመብራት መቋረጥ ምክንያት 81ኛው ደቂቃ ላይ ቆሞ የነበረው የኢትዮጵያ እና ደቡብ ሱዳን ሴት ብሔራዊ ቡድኖች ጨዋታ ዛሬ ረፋድ ላይ ቀሪ ደቂቃዎች ተደርጎ ኢትዮጵያ 2 ተጨማሪ ጎል አስቆጥራ 11 ለ 0 ተጠናቋል፡፡

በዛሬ ረፋዱ ጨዋታ ሎዛ አበራ 86ኛው እና 90ኛው ደቂቃ ላይ ከሴናፍ ዋቁማ የተመቻቹላትን ኳሶች አስቆጥራለች፡፡

ደቡብ ሱዳን ላይ 7 ጎሎች ያስቆጠረችው ሎዛ አበራ በኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ታሪክ በአንድ ጨዋታ በርካታ ጎል ያስቆጠረች ተጫዋችም ሆናለች።

እንደሶከር ኢትዮጵያ ዘገባ የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ደቡብ ሱዳንን 11-0 ማሸነፉን ተከትሎም በታሪኩ ትልቁን ድል አስመዝግቧል።

ሉሲዎቹ ከዚህ ቀደም በ2018 ሊቢያን ፤ በ2019 ጅቡቲን በተመሳሳይ 8-0 ያሸነፉበት ውጤት ከፍተኛው ሆኖ ቆይቷል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.