Fana: At a Speed of Life!

ምርጫው በሰላም ተጠናቋል – የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 16 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) 6ኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ በሰላም መጠናቀቁን የፌደራል ፖሊስ አስታወቀ፡፡

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደመላሽ ገብረሚካኤል በሰጡት መግለጫ ምርጫው በሰላም መጠናቀቁን ተናግረዋል።

የምርጫውን ሂደት ለማደናቀፍ የተወሰኑ ቦታዎች ላይ ሙከራ መደረጉን ያነሱት ኮሚሽነሩ፥ ይሁን እንጅ ሙከራው በፀጥታ ሃይሉ መክሸፉን ገልጸዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም በሁለት የምርጫ ጣቢያዎች በተፈጠረ ሁከት ፀረ ሰላም ሃይሎችን መደምሰስ መቻሉንም ነው የተናገሩት፡፡

በህግ ማስከበር ሂደቱ የፀጥታ አስከባሪ አካል ህይወት ማለፉንም አንስተዋል፡፡

በአጠቃላይየምርጫውን ሂደት ለማወክ የሞከሩ 123 ሰዎች በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን፥ 42ቱ ላይ ቀላል ቅጣት ተላልፎባቸዋል ብለዋል፡፡

ለምርጫው ሰላማዊ ሂደት የህዝቡ ትብብር፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ለውድድር ብቻ ተዘጋጅቶ መውጣት፣ በቴክኖሎጅ የታገዘና የተጠናከረ የፀጥታ ስራ መሰራቱ አስተዋጽኦ አበርክቷልም ነው ያሉት፡፡

ኮሚሽኑም በድህረ ምርጫ ሊከሰት የሚችል የፀጥታ ችግርን ለከመከላከል ሙሉ ዝግጅት አድርጌያለሁ ብሏል፡፡

የፀጥታ ስራው የፌደራል ፖሊስ፣ የደህነት ተቋማትናና የክልል የፀጥታ አካላት ጋር በቅንጅት የተሰራ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡

በሃይለኢየሱስ ስዩም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.