Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

አርባ ምንጭ ከተማ ዳግም ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ተመለሰ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አርባ ምንጭ ከተማ ዳግም ወደ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ተመልሷል። በ23ኛ ሳምንት ምድብ "ለ" ተጠባቂ ጨዋታ አርባ ምንጭ ከተማ ቦዲቲ ከተማን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡ ውጤቱን ተከትሎም አርባ ምንጭ ከተማ ሶስት ጨዋታዎች እየቀሩት ከአንድ የውድድር ዘመን በኃላ ዳግም ወደ ፕሪሚየር ሊጉ መመለሱን አረጋግጧል፡፡ አርባ ምንጭ ከተማ በ2015 የውድድር ዘመን ከፕሪሚየር ሊጉ ወደ ከፍተኛ ሊግ መውረዱ የሚታወስ ሲሆን÷ በዓመቱ ወደ ሊጉ መመለስ መቻሉንም የክለቡ መረጃ ያመላክታል፡፡
Read More...

በሻምፒየንስ ሊጉ ግማሽ ፍፃሜ ዶርትመንድና ፓሪስ ሴንት ጀርሜይን ይፋለማሉ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የጀርመኑ ቦርሺያ ዶርትመንድና የፈረንሳዩ ፓሪስ ሴንት ጀርሜይን በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ግማሽ ፍፃሜ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታቸውን ዛሬ ምሽት ያካሂዳሉ፡፡ ጨዋታው ከምሽቱ 4 ሰዓት በዶርትመንድ ሜዳ ሲገናል ኤዱና ፓርከ የሚካሄድ ሲሆን÷ የመልሱ ጨዋታ ደግሞ በፓሪስ ፓርክ ደ ፕሪንስ የሚካሄድ ይሆናል፡፡ ትናንት ባየርን ሙኒክ…

በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ግማሽ ፍፃሜ ዛሬ ተጠባቂ ጨዋታ ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ ምሽት በሚካሄደው የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ግማሽ ፍፃሜ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታ ሪያል ማድሪድ ከባየርን ሙኒክ ይፋለማሉ፡፡ ጨዋታው ከምሽቱ 4:00 ጀምሮ በባየር ሙኒክ ሜዳ አሊያንዝ አሬና ሲካሄድ፤ የመልሱ ጨዋታ ደግሞ ቀጣይ ሳምንት በሪያል ማድሪድ ሜዳ ሳንትያጎ ቤርናባው ይካሄዳል። በሻምፒዮንስ ሊጉ…

አርሰናል ቶተንሃምን በማሸነፍ የዋንጫ ተፎካካሪነቱን አጠናክሯል

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በተጠባቂው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሰሜን ለንደን ደርቢ አርሰናል ቶተንሃምን 3 ለ 2 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡ 10 ሰዓት ላይ በተደረገው ጨዋታ የአርሰናልን የማሸነፊያ ግቦች ሳካ፣ ሀቨርተስ እና ሆይቤር (በራሱ ግብ ላይ) አስቆጥረዋል፡፡ ቶተንሃምን ከሽንፈት ያላዳኑትን ግቦች ደግሞ ሮሜሮ እና ሰን አስቆጥረዋል፡፡…

ማንችስተር ዩናይትድ ከበርንሌይ አቻ ሲለያይ ሼፍልድ ዩናይትድ መውረዱን አረጋገጠ 

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ በተደረጉ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ኒውካስልና ዎልቭስ ተጋጣሚዎቻቸውን ሲያሸንፉ ማንችስተር ዩናይትድ አቻ ተለያየ፡፡ ከቀኑ 11 ሰዓት ላይ በተደረጉ ጨዋታዎች ኒውካስል ሼፍልድ ዩናይትድን 5ለ1 በሆነ ሰፊ ውጤት ሲያሸንፍ ዎልቭስ ሉተንን 2ለ1 ረትቷል፡፡ በሜዳው በርንሌይን ያስተናገደው ማንችስተር ዩናይትድ…

በፕሪሚየርሊጉ ሊቨርፑል ወሳኝ ነጥብ ጥሏል

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የእንግሊዝ ፕሪሚየርሊግ የዋንጫ ተፎካካሪ የነበረው ሊቨርፑል ከዌስትሃም ጋር ሁለት አቻ ተለያይቷል፡፡ በምሳ ሰዓት በተደረገው ጨዋታ ጃሮድ ቦውን እና ሚሸል አንቶኒዮ የዌስተሃም ጎሎችን ሲያስቆጥሩ አንዲ ሮበርትሰን እና አልፌንሴ አሪዮላ(በራሱ ላይ) የሊቨርፑል ጎሎችን አስቆረዋል፡፡ ውጤቱን ተከትሎም በቅርቡ ከዩሮፓ ሊግ…

በሻንጋይ ዳይመንድ ሊግ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከ1 እስከ 4 በመሆን አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሻንጋይ ዳይመንድ ሊግ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከአንደኛ እስከ አራተኛ ያለውን ደረጃ በመያዝ በበላይነት አጠናቀዋል፡፡ በውድድሩ በሴቶች የ5 ሺህ ሜትር ውድድር መቅደስ ዓለምሸት 14 ደቂቃ ከ36 ሰከንድ በመግባት አሸንፋለች፡፡ አያል ዳኛቸው ከባድ ፉክክር አድርጋ በ16 ማይክሮ ሰከንድ ተቀድማ ሁለተኛ ደረጃን ስትይዝ ፥…