Fana: At a Speed of Life!

በፕሪሚየርሊጉ ሊቨርፑል ወሳኝ ነጥብ ጥሏል

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የእንግሊዝ ፕሪሚየርሊግ የዋንጫ ተፎካካሪ የነበረው ሊቨርፑል ከዌስትሃም ጋር ሁለት አቻ ተለያይቷል፡፡

በምሳ ሰዓት በተደረገው ጨዋታ ጃሮድ ቦውን እና ሚሸል አንቶኒዮ የዌስተሃም ጎሎችን ሲያስቆጥሩ አንዲ ሮበርትሰን እና አልፌንሴ አሪዮላ(በራሱ ላይ) የሊቨርፑል ጎሎችን አስቆረዋል፡፡

ውጤቱን ተከትሎም በቅርቡ ከዩሮፓ ሊግ የተሰናበተው ሊቨርፑል እስከመጨረሻው የፕሪሚየርሊጉ የዋንጫ ተፎካካሪ የመሆን እድሉ አጣብቂኝ ውስጥ ገብቷል፡፡

ሊቨርፑል 75 ነጥቦችን በመያዝ በደረጃ ሰንጠረዡ 3ኛ ላይ ሰቀመጥ አርሰናል በ77 ማንቼስተር ሲቲ ደግሞ በ76 ነጥብ  አንደኛ እና ሁለተኛ ሆነነው ሊጉን እየመመሩ ይገኛሉ፡፡

የፕሪሚየርሊጉ ጨዋታዎች ምሽት መካሄዳቸውን ሲቀጥሉ ማንቸሰተር ዩናትድ ከበርንሌይ፣ቼልሲ ከአስቶንቪላ፣ኒውካስትል ከሼፊልድ፣ፉልሃም ከክሪስታል ፓላስ፣ወልቭስ ከሉተን እንዲሁም ኤቨርተን ከብረንትፎርድ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.