Fana: At a Speed of Life!

ማንችስተር ዩናይትድ ከበርንሌይ አቻ ሲለያይ ሼፍልድ ዩናይትድ መውረዱን አረጋገጠ 

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ በተደረጉ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ኒውካስልና ዎልቭስ ተጋጣሚዎቻቸውን ሲያሸንፉ ማንችስተር ዩናይትድ አቻ ተለያየ፡፡

ከቀኑ 11 ሰዓት ላይ በተደረጉ ጨዋታዎች ኒውካስል ሼፍልድ ዩናይትድን 5ለ1 በሆነ ሰፊ ውጤት ሲያሸንፍ ዎልቭስ ሉተንን 2ለ1 ረትቷል፡፡

በሜዳው በርንሌይን ያስተናገደው ማንችስተር ዩናይትድ አንድ አቻ የተለያየ ሲሆን ፥ ፉልሃምና ክርስታል ፓላስ ያደረጉትም ጨዋታ አንድ አቻ በሆነ ውጤት ተጠናቋል፡፡

ቀደም ብሎ ሊቨርፑልና ዌስትሃም ያደረጉት ጨዋታ ሁለት አቻ መጠናቀቁን ተከትሎ የሊቨርፑል ዋንጫ የማንሳት ተስፋ አጣብቂኝ ውስጥ ገብቷል፡፡

የሊጉን የደረጃ ሰንጠረዥ አርሰናል በ77 ነጥብ ሲመራ ማንችስተር ሲቲ በ76 ነጥብ ሁለተኛ ፥ ሊቨርፑል ደግሞ በ75 ነጥብ ሦስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.