Fana: At a Speed of Life!

በሃገሪቱ የ10 ዓመት መሪ የልማት እቅድ ውስጥ እየተካሄደ ያለው ውይይት እንደቀጠለ ነው

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 3፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሃገሪቱ የ10 ዓመት መሪ የልማት እቅድ ውስጥ እየተካሄደ ያለው ውይይት እንደቀጠለ ነው።

በዛሬው እለትም ትሉረቱን በቱሪዝም ዘርፍ ላይ ያደረገው ውይይት እየተካሄደ ነው።

በመሪ እቅዱ የቱሪዝም ዘርፉ የእስካሁን ችግሮችና በቀጣይ 10 ዓመት ዘርፉን ውጤታማ በማድረግ የሚገኙ ትሩፋቶችና የሚከናውኑ ተግባራት ቀርበው ውይይት እየተደረገባቸው ይገኛል።

በትናንትናው ዕለትም የንግድና ኢንዱስትሪ ዘርፍ የቀጣይ 10 ዓመት እቅድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።

ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል የሃገሪቱ የንግድ ስርዓት ዘመናዊና አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ስምምነቶችን ወደ ውጤት የሚለውጡበት እንደሚሆን ተናግረዋል።

ለዚህም የአፈፃፀም ክፍተቶች የዕቅድን ስኬታማነት እንዳይቀንሱ በትኩረት ይሰራል ብለዋል።

በሶዶ ለማ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.