Fana: At a Speed of Life!

በህወሓት አውሬነት በነፍስ ግቢ ነፍስ ውጪ ስቃይ ውስጥ ያለፉት ነፍሰ ጡሮች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)አሸባሪው ህወሓት ፈጽሞ የማይራራና አረመኔ መሆኑ በወረራቸው ቦታዎች አስመስክሯል።

በማይራራውና ሰብዓዊ ፍጡር የማያደርጋቸውን ሁሉ ከአማራ ክልል በወረራቸው ቦታዎች ህፃናት፣ ሴቶችን፣ ነፍሰጡሮችን፣ የሃይማኖት አባቶችንና አዛውንቶችን መግደል፣ ማሳደድና መድፈር የእኩይ ድርጊቶቹ መገለጫዎቹ ስለመሆኑ በቂ ማሳያዎች አሉ።

አሸባሪው ከቀያቸው ካፈናቀላቸውና ለከፋ ህይወት ከዳረጋቸው ዜጎች መካከል ወይዘሮ መሠረት ሰማው አንዷ ስትሆን በደሴ ከተማ በአንዱ የተፈናቃዮች መጠለያ ውስጥ ትገኛለች።

እርሷ ከኀዘን ወደ ኀዘን የተሸጋገርኩበት ዓመት ላይ ነኝ ያለች ሲሆን÷ ራያ ቆቦ 01 ከሚባለው አካባቢ ነው የመጣችው።

ሁለት ቀን በእግሯ ተጉዛ ሌላውን ደግሞ በባጃጅ ገሚሱን ደግሞ ሰዎች እየተሸከሟትና እየደገፏት ነበር ነፋሷን ለማትረፍ ከሁለት ልጆቿ ጋር ቀድሞ ወደማታውቀው ደሴ ከተማ የመጣችው።

በአሁኑ ወቅት የዘጠኝ ወር ነፍሰ ጡር ናት።

ያለማቆም በሁለት ዓይኖቿ እንባ እንደጉድ ይወርዳል፤ ‘‘ከሁለት ወር በፊት ልጄን በመኪና አደጋ ተነጠቅሁ፤ ኀዘኔን አልጨረስኩም፤ ዳሱ እንኳን አልፈረሰም ነበር’’ ትላለች።

‘‘ኀዘን ላይ እያለሁ ሌላ ኀዘን መጣብኝ፤ ወረ ግቡ ብሆንም የሚረዳኝ ባለመኖሩ እዚህ ከመጣሁ ጀምሮ አንድም ቀን ሃኪም ቤት ሄጄ አልታከምኩም’’ ትላለች።

ወይዘሮ መሠረት ከቤት ስትወጣ አንዲትም የቅያሬ ልብስ አልያዘችም።

የትዳር አጋሯ እና ቤተሰቦቿ በሙሉ ራያ ቆቦ ውስጥ እንደተከበቡ መቅረታቸውንና ህዝቡ ለርሃብ ከመጋለጡም በላይ በርካቶች መሞታቸውን ከሁኔታው ያመለጡ ሰዎች ነግረዋታል።

ቤተሰቦቿም በምን ሁኔታ ላይ እንዳሉ ማወቅ አልቻለችም።

በአሸባሪው ህወሓት የዚህን ያህል የከፋ ሥራ ይሰራል ብላ አስባ የማታውቅ ሲሆን÷ ግን በቃ ሆነ! ነገሮች ሁሉ አስደንጋጭና እንግዳ ሆነውባታል።

መሠረት እስካሁን ህክምና ባትሄድም ሰሞኑን ለህክምና ይረዳት ዘንድ አቶ ወርቁ አይተነው የተባሉ ባለሀብት የተወሰነ ገንዘብ ስለሰጡኝ ሃኪም ቤት እሄዳለሁ፤ ለልጆቼም ቅያሬ ልብስ እገዛለሁ በማለት ሰጪውን ማመስገኗን ኢፕድ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.