Fana: At a Speed of Life!

በህዳሴ ግድብ ዙሪያ አራተኛ አደራዳሪ አካል እንዲገባ የሚቀርበው ጥያቄ ትርጉም የለሽ ነው – የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ የሶስትዮሽ ድርድሩ ባልተቋጨበት አራተኛ አደራዳሪ አካል እንዲገባ የሚቀርበው ጥያቄ ትርጉም የለሽ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።

የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በሰጡት መግለጫ ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ህብረት መራሹ የሶስትዮሽ ድርድር አክብሮት አላት ብለዋል ።

አሁን ላይ የሶስትዮሽ ድርድሩ በአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር የስልጣን ሽግግር ምክንያት ለጊዜው መቋረጡንም ጠቅሰዋል ።

የህብረቱን ሊቀመንበርነት ከደቡብ አፍሪካ የተቀበለችው ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ሶስቱንም ሀገራት በድርድሩ ዙሪያ በተናጠል ማናገሯን ገልጸዋል ።

አሁን ያለው ድርድር ውጤታማ መሆን አለመሆኑ ሳይታወቅ ሌላ ድርድር መጥራት ተገቢነት እንደሌለውም ቃል አቀባዩ ገልጸዋል ።

ድርድሩ ውጤታማ ባይሆን እንኳ የሚመራው በፈረንጆቹ 2015 በመሪዎች ደረጃ በተደረሰው የመርሆዎች ስምምነት በተቀመጠው መንገድ ይሆናልም ብለዋል ቃል አቀባዩ፡፡

በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ መጥተው የነበሩት የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን መልዕክተኛ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን እንዲሁም ከሰብዓዊ መብት ኮሚሽነር ጋር መወያየታቸውን አውስተዋል።

በውይይቱ ወቅት የኢትዮጵያ መንግስት ስላካሄደው የህግ ማስከበር ዘመቻ እና ሰብዓዊ ድጋፍ ገለጻ መደረጉን አስረድተዋል።

በትግራይ ክልል ሰብዓዊ ድጋፍ ለማቅረብ በርካታ የረድኤት ድርጅቶች ጥያቄ ማቅረባቸውን ያነሱት ቃል አቀባዩ፥ ድርጅቶቹ ወደ ተግባር ሲገቡ ግን ባቀረቡት ጥያቄ ልክ አለመሆኑን ጠቁመዋል፡፡

አሁን በረድኤት ድርጅቶች እየቀረበ ያለው ድጋፍ ከ30 በመቶ የበለጠ አለመሆኑን እና 70 በመቶው እየቀረበ ያለው በመንግሥት በኩል መሆኑንም አስታውሰዋል።

በዓላዛር ታደለ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.