Fana: At a Speed of Life!

በህገ ወጥ መንገድ ወደ ሃገር ውስጥ ሊገባ የነበረ የኮንትሮባድ እቃ ተያዘ

አዲስ አበባ ፣መስከረም 4፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በምስራቅ ሐረርጌ ዞን ባቢሌ ከተማ ከ2 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች መያዛቸውን ፖሊስ አስታወቀ፡፡

የዞኑ ፖሊስ ኮሚሽን የኮሙዩኒኬሽንና ሚዲያ ዲቪዥን ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ቶሎሳ ጎሹ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት÷ የኮንትሮባንድ እቃዎቹ ትናንት ሌሊቱ ከቦምባስ ከተማ ወደ ባቢሌ ከተማ በአይሱዙ የጭነት ተሸከርካሪ ተጭኖ ሊገባ ሲል ባቢሌ ከተማ መግቢያ ላይ ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ መያዝ ተችሏል፡፡

የኮንትሮባንድ እቃዎቹም 2 ሚሊየን 300 ሺህ 150 ብር ግምት እንዳላቸው ተገልጿል፡፡

በህገ ወጥ መንገድ ሲጓጓዝ የተያዙት እቃዎች የባለሦስት እግርና የተለያዩ ተሸከርካሪዎች ጎማዎችና መለዋወጫዎች፣ የተሸከርካሪ የሞተር ዘይቶች፣ የህፃናትና የአዋቂ አልባሳትና ጫማዎች፣ሽቶዎች፣ የሞባይል ስልኮች እንዲሁም የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ናቸው፡፡

ዋና ኢንስፔክተር ቶሎሳ ጎሹ እቃዎቹን በህገወጥ መንገድ ሲያጓጉዝ የነበረው አሽከርካሪ ለጊዜው ማምለጡንና በፖሊስ ክትትል እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በተሾመ ኃይሉ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.