Fana: At a Speed of Life!

በመቅደላ ወረዳ የተገነቡ መሰረተ ልማቶች ተመረቁ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 15፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን መቅደላ ወረዳ የተገነቡ የተለያዩ መሰረተ ልማቶች በዛሬው ዕለት ተመርቀዋል።

በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን እና የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ተመስገን ጥሩነህን ጨምሮ የፌዴራል እና የክልሉ መንግስት ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች እንዲሁም የአካባቢው ነዋሪወች ተገኝተዋል።

የመቅደላ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ተፈራ ሞላ እንደገለጹት ፥ ዛሬ ከተመረቁት መሰረተ ልማቶች መካከል የመቅደላ ማሻ የመጀመሪያ ደረጀ ሆስፒታልና የመቅደላ ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ ይገኙበታል።

የደቡብ ወሎንና ደቡብ ጎንደር ዞኖችን የሚያገናኘው “በበሽሎ” ወንዝ ላይ የተሰራው 150 ሜትር ርዝመት ያለው ድልድይም ዛሬ ከተመረቁት መሰረተ ልማቶች መካከል አንዱ መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል።

የድልድዩ ግንባታ ሁለቱን ዞኖች ከማገናኘቱ ባለፈ የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ትስስሩን ማጠናከር የሚያስችል መሆኑ ተመላክቷል።

ከሰዓት በኋላም አመራሮቹ በማሻ ስታዲዮም ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር በልማት፣ በመልካም አስተዳደርና በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር ማድረጋቸው ተገልጿል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.