Fana: At a Speed of Life!

በመቐለ ከተማ በ4 ቢሊየን ብር ወጪ የተገነቡ መሰረተ ልማቶች ተመረቁ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 7፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በትግራይ ክልል መቐለ ከተማ በ4 ቢሊየን ብር ወጪ የተገነቡ መሰረተ ልማቶች ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ሆኑ፡፡

45ኛ ዓመት የህወሓት ምስረታ በዓልን ምክንያት በማድረግ በመቐለ ከተማ በ4 ቢሊየን ብር ወጪ የተገነቡ መሰረተ ልማቶች በዛሬው ዕለት ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ሆነዋል፡፡

በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረፂዮን ገብረሚካኤል፣ የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ ወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሂም፣ የክልሉ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ሩፋኤል ሺፋረ እና ሌሎች የክልሉ እና የከተማዋ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

መሰረተ ልማቶቹ በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች የተገነቡ የአስፓልት መንገዶች እና የአግዓዚ አደባባይ መሆናቸው ተመላክቷል።

ከምረቃ መርሃ ግብሩ በኋላም አመራሮች በአግዓዚ አደባባይ የችግኝ ተከላ ስነ-ስርዓት አከናውነዋል።

በተያያዘ ዜና በከተማዋ በ1ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ወጪ ለሚገነቡ ሆስፒታሎች፣ ዘመናዊ መናኸሪያ፣ ትምህርት ቤቶች እና ለሌሎች መሰረተ ልማቶች ትናንት የመሰረት ድንጋይ ተቀምጧል፡፡

በዮናታን ግዛቸው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.