Fana: At a Speed of Life!

በመተከል ዞን ቡለን ወረዳ በቅርቡ በተፈጠረው የጸጥታ ችግር ከቄያቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች ከ18 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ቡለን ወረዳ በቅርቡ በተፈጠረው የጸጥታ ችግር ከቄያቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች ከ18 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው ድጋፍ ተደረገ፡፡
የድጋፉ ርክክቡ የአማራ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ፣ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሃሰን ፣ የገቢዎች ሚኒስተር አቶ ላቀ አያሌው ፣ የፌደራል ጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ደበ
ቀበታ እና ሌሎች የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት መካሄዱ ታውቋል፡፡
በፌዴራል ጉምሩክ ኮሚሽንና በገቢዎች ሚኒስቴር በኩል የቀረበውን የምግብ እህል ድጋፍም የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ተረክቧል፡፡
ድጋፉ የምግብና ምግብ ነክ ቁሳቁሶች ሲሆን አጠቃላይ ወጭው ከ18 ሚሊየን ብር በላይ እንደሆነ የፌደራል ጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ደበቀበታ ተናግረዋል።
የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ተመስገን ጥሩነህ የሁለቱን ክልል ህዝቦች አብሮነትን በማይፈልጉ ጸረ ሰላም ሃይሎች ምክንያት የተፈናቀሉ ዜጎችን በዘላቂነት ለማቋቋም በትኩረት እንደሚሰራም ገልጸዋል።
የቤኒሻንጉ ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሃሰን በበኩላቸው በዞኑ ውስጥ የተፈጠረውን ችግር ከጸጥታ ሃይሎች ጋር በትብብር የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደ ነበሩበት ከመመለስ ባሻገር የሚደረገው ሰብዓዊ ድጋፍም ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
ድጋፉ የተደረገው በሀገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች በኮንትሮባንድ ሲንቀሳቀስ በጉምሩክ ኮሚሽን አማካኝነት የተያዙ የምግብና ምግብ ነክ ቁሶች መሆናቸውን ከመተከል ዞን ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.